ከወርቅ ምርት 63 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር መገኘቱ ተገለጸ
በ2016 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከወርቅ ምርት 63 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማዕድን ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን ገምግሟል። በሩብ ዓመቱ 996 ነጥብ 1 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማግኘት ታቅዶ 719 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም በኩባንያዎች ተመርቶ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ …